ሻይ ኮረንቲ – ክፍል ሁለት

እናንተ? ሁለተኛውን ክፍል አዘገየሁባችሁ አይደል?

ምን ታመጣላችሁ!!!!

የምር ስወዛገብ ነበር … በሀሳብ! ይኼ ኮሮና እኮ…. እናላችሁ … “በዚህ በጭንቅ ጊዜ አሁን እነዚህ ሦስት ሰዎች ስለ ወሲብ ሲያወሩ ማን መስማት ይፈልጋል?” በሚል ፍርሃት እና “ ሁሉ ነው ስለ ኮሮና የሚያወራው … እንዲያውም አዕምሮን ትንሽ ከዛ ጭንቅ ለተወሰኑ ደቂቃዎችም ቢሆን ፈታ የሚያደርግ ነገር ብናነብ?” በሚል መሟገቻ ስወዛገብ ቆይቼ …. ይኸው ዛሬ ከመሸ ወስኜ … ሁለተኛው ሙግቴ አሸንፎ … ከባለፈው የቀጠለውን ውይይታችንን እነሆ!

ራሳችንን እና ሌሎችን ከ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየጠበቅን ፣ አስፈላጊዎቹን መሰናዶዎች እያደረግን ፣ መከተል ያሉብንን አካሄዶች እየተከተልን … ደህንነታችንን እንድንጠብቅ አደራ እላለሁ፡፡

(ካለፈው የቀጠለ)

ዊሊ፡  አንዳንዴ ደግሞ … ሳስበው … በሴክስ ጊዜ የሚኖሩ ገደቦች … ፈልገህ እንኳን እያደረግኸው … የሰዎች ፍላጎት በጣም የተለያየ ነውና … እንደሚባለው ወሲባዊ ነፃነትን የሚያጠፉ መስሎ አይሰማኝም፡፡ ብዙ እያወቅህ ስትመጣ ራስህን ነፃ ለማድረግ አትቸገርም፡፡ ለምሳሌ እኔ ከራሴ ልምድ…. መጀመሪያ ላይ ሰው ማግኘት ምናምን ስጀምር … ማንኛውንም አይነት ሴክስ ለማድረግ ፈቃደኛ አልነበርኩም፡፡ ምንም የማውቀው ነገር ስላልነበረ ማለት ነው፡፡ ከዛ ራሴን እያስተማርኩ … እያወቅሁ ስመጣ … ከመደበኞቹ ሮል ወይም ወሲባዊ ሚና የተለየውን … ሳይድ የሚባለውን … ከ ፔኔትሬቲቭ ሴክስ የፀዳ ሴክስን እየለመድኩ መጣሁ፡፡ ከዛ ቀስ በቀስ … ሌሎች ሚናዎችንም እየሞከርኩ አይቻለሁ፡፡ ከዛ በስተመጨረሻ የደመደምኩት ነገር ግን ምንድን ነው…. ሴክስ ማለት ሁለት ሰዎች እኔ እንዲህ ነኝ …ወይም አደርጋለሁ ብለው የሚናገሩት ነገር ሳይሆን… ስሜት ለስሜት ተናብበው … እዛ ቦታ ላይ… አብረው የሚፈጥሩት … ራሱን የቻለ … ቀድመው define የማያደርጉት ክስተት ነው፡፡ ነፃነቱ ሲኖርህ … ቦተም ነኝ ወይም ቶፕ ነኝ ብለህ ራስህን ላትገድበው ትችላለህ፡፡ መሳሳቡ ሲኖር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ … ሲጀመር ያንን አስተሳሰብ … ቅድመ ሁኔታ ይዘው ሲመጡ ግን … ሰዎች ሴክስን በነፃነት እንዲተገብሩት እድል አይሰጣቸውም፤ ይግባቸዋለ ማለት ነው፡፡ አንድ ቶፕ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሰው … ቅድመ ጨዋታዎች ላይ በነፃነት ሊሳተፍ አይችል ይሆናል … ቁጡን ስትነካው… አትንካኝ ብሎ ሊነሳ ሁሉ ይችላል … እነዚህ ገደቦች ደግሞ ሌላኛውን ሰው ስሜቱን ሊያጠፉት ይችላሉ … እና ስለ ሴክስ ያለንን ዕውቀት እያሰፋን ካልመጣን … የሆነ ጥግ ላይ ቆመን እንቀራለን፡፡

ቤን፡  በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን … የአንዳንድ የኮሚኒቲያችንን አባላት ሴክሹዋል ነፃነት… ማለትም… ያለ ምንም ኢሞሽናል…

ዳኒ፡  ዕድር አደረግከው እኮ (ዳኒ አቋረጠኝ)

ቤን፡   ማለት…

ዊሊ፡   ሃሃሃሃሃሃ

ዳኒ፡   የኮሚኒቲያችንን አባላት ስትል ነዋ… ሃሃሃሃ

ቤን፡  ሃሃሃሃ……ፖለቲካ …  አመዳም!!!

ቤን፡  ብቻ…. የአንዳንድ ሰዎችን … ሴክስን ያለምንም ኢሞሽናል ቅርርብ … ፍላጎትን … ቅድም ተፈጥሮአዊ ፍላጎት ነው ብለን የለ? … ያንን ተፈጥሮአዊ ፍላጎት ለማሟላት ብቻ … ምንም ዓይነት ከዛ ያለፈን ነገር ሳይሹ … ሚናቸውን ለይተው … ቦተም ወይም ቶፕ ነኝ በለው አሳውቀው ለወሲብ የሚስማማቸው ሮል ያለውን የሚፈልጉትን … ነፃነታቸውንም እንዳንዘነጋው ወይም እንዳንጨቁነውም መጠንቀቅ አለብን፡፡ እንዲያውም ኮንሰንት ነው ይኼ በራሱ ፤ ይኼንን ነኝ … ይኼንን ከሆንክ እን*ባዳ አይነት ፊትለፊት የሆነ ጥያቄ የሚያስደስታቸው እና … ምንም ዓይነት ከመግባት መውጣት የዘለለ የስሜት ግንኙነት የማይፈልጉ የተለያየ ሚና ያላቸው ሰዎችም አሉና … የእነሱንም ነፃነት … ሴክስ የሁለት ሰዎች በስሜት መቧደን ነው ብለን እንዳንደመድመው ለማስታወስ ነው፡፡ የሚፈልጉትን ነገር አውቀው ተነጋግረው ፣ ተስማምተው እስካደረጉት ድረስ ….

ዳኒ፡  አንዳንዴ ምን ያናድደኛል መሰለህ… ይኼ አሁን ያወራነው ነገር ሁሉ ተግባራዊነቱ ለእኛ ለዜጋው ኮሚኒቲ ብቻ አይደለም ፤ ለሁሉም … ለ አጠቃላይ ህብረተሰቡ ነው፡፡ በአጠቃላይ የሰው ሁሉ ችግር ነው፡፡ አሁን ለምሳሌ፡ ብዙ ጊዜ ስለ ኤች አይቪም ይሁን… ስለ ወሲባዊ ፈቃድም ይሁን .. ሌላም ሌላም ጉዳይ ሲወራ ፣ ሰዎች እኛ ጋር ብቻ ያለ ችግር ሊመስላቸው ይችላል፡፡ አይደለም፡፡ ሁሉም ዘንድ ያለ ችግር ነው፡፡ እኛ ጋር ለየት የሚለው … በግልፅ እያወራንበት አይደለም ነው፡፡ ያ ነው ችግሩ፡፡ እንጂ … ሰዎች .. ዜጎች እንዲህ ናቸው ፣ የዜጋ ሴክስ ልቅ ነው ፣ ፈቃድ የለበትም …. እያሉ እንዲፈሩ እና ከዜጋው ማህበረሰብ እንዲለዩ ወይም እንዲርቁ አልፈልግም፡፡ ይኼ የሰው ልጅ ችግር ነው፡፡ ቀጥ ሆነ ዜጋ፡፡

ቤን፡   ስለዚህ … አሪፍ የሴክስ experience እንዲኖን … የምንፈልገውን እንወቅ ፣ የምንፈልገውን እንናገር ፣ እና…. በቃ…. ጌት ዳውን! ሃሃሃ

ዳኒ፡   በቃ! አጋራችንን እናድምጥ… እንስማ ነው!

ቦቼ፡  እኔ አንድ ጥያቄ አለኝ፡፡ ለምሳሌ አሁን… ሁለት ሰዎች ሴክስ እያደረጉ… አንደኛው በመሃል ማቆም ቢፈልግ (ሴክሱን ነው ደሞ .. ሃሃ) … ያ ነገር እንዴት ነው የሚሆነው? ተፈቃቅደው … ተስማምተው ከጀመሩ በኋላ .. የሀሳብ መቀየር ቢኖር … እንዲህ ያለው ነገር እንዴት ነው የሚስተናገዱት?

ቤን፡  እኔ እንዲያውም እንደዛ አይነት አጋጣሚ አለኝ፡፡ ልንዋሰብ ተስማማን … ተፈላለግን ፣ ተገናኘን፡፡ ነገር ግን በመሃል … ሁለታችንም ምቶታችን የምንፈልገው ደረጃ ላይ አልነበረም፡፡ እና Anal አቁመን በእጅ እና ጨረስን፡፡ ብዙ አማራጮች አሉን እኮ፡፡ ቅድምም አውርተንባቸዋል… ሴክስ የምንላቸውን ነገሮች፡፡ አንዳችን እንኳን ካልተመቸን እኮ ያኛውም ሰው ይደሰትበታል የሚል እምነት የለኝም ፤ ሌላ ፌቲሽ ምናምን ያለበት ሰው ካልሆነ፡፡ ሃሃ

ቦቼ፡  ግን… ምናልባት አንደኛው ምንም አይነት ንክኪ የማይፈልግ ከሆነስ? ለምሳሌ… አንዳንዴ ተመሳሳይ የሆኑ ነገሮችን እሰማለሁ ሰዎች … የንፅህና ጉድለት ሴክስ መሀል ላይ የወሲብ ስሜታቸውን ሊያጡት ይችላሉ፡፡ እና ያ ነገር በኮንሰንት ውስጥ የሚያልፍ ወይም ማለፍ ያለበት ነገር ነው? .. ወይስ… ምንድን ነው?

ቤን፡  እኔ ከኮንሰንት ጋር የሚገናኝም አይመስለኝም፡፡ ከዛም በላይ ነው…. እንዲያውም ሰው በደንብ እንዲያውቀው … በተለይም ዜጋው እንዲያውቀው የምፈልገው ነገር …. Shit Happens!

ዳኒ፡   Literally… ሃሃ

ቤን፡  ፊንጢጣ ሰውነታችን የምንበላውን ምግብ ፣ የሚፈልገውን ተጠቅሞ የማይፈልገውን የሚያስወግድበት ቦታ ነው! እና ምንም ያህል ዱሽ አድርገህ … አፅድተህ ብትሄድ … በሆነ አጋጣሚ ሊያጋጥም ይችላል፡፡

 ዊሊ፡   እንዴ … ዱሽ አድርገህም እኮ … በጥድፊያ ሊሆን ይችላል … በደንብ ያልወጣ ውሃም ሊያጋጥም ይችላል፡፡

ቤን፡   ሃሃ… ምነው አቋረጥከኝ … ደርሶብሃል እንዴ?

(ሳቅ በሳቅ)

ዊሊ፡   እሰይ! … ቢደርስብኝስ

ቤን፡   ሃሃ… እና… ይኼ ነገር ባናስታውሰው እንኳ… ከጭንቅላታችን ውስጥ መጥፋት የለበትም፡፡ ይኼ በእምስ የሚደረግ ሴክስ አይደለም … በእምስ የሚደረግ ሴክስ ራሱ … የራሱ የሆነ ዝግጅቶች ይኖሩታል፡፡ እና… የወሲብ ስሜትህን ሊያጠፋው ይችል ይሆናል ፤ ግን አብሮህ ያለውን ፣ የአጋርህን ስሜት በሚጎዳ መልኩ መጠየፍ አለብን ብዬ አላምንም፡፡

ቦቼ፡   ልክ ነው፡፡ ገብቶኛል፡፡ ግን … በዛን ጊዜ … አሁን ያወራነው በሚያጋጥም ጊዜ ቦተሙ ሰው ስሜት ላይ ቢሆንና ሴክስ ማድረግ ማቆም ባይፈልግስ … ኮንሰንት ወይም ፈቃድ አናል ሴክስ ለማድረግ ብቻ አይደለም … በዚህ አጋጣሚም ምን እንደሚፈጠር መነጋገር አለባቸው? ወይስ … የማን ሃላፊነት ነው? … እንዲህ ያሉ ነገሮች

ዊሊ፡   እኔ ሳስበው … ቅድም ያልኩት የኮኔክሽን .. በስሜት የመሳሳብ ጉዳይ የሚጠቅመው ለዚህ ነው፡፡ ስትግባባ … በግልጽ ትነጋገራለህ፡፡ የማልፈልጋቸው ነገሮች ካሉ እንዴት መታረም እንዳለባቸው በግልፅ መነጋገር አለብን ብዬ አስባለሁ፡፡ የቦተምነት ሚና ኖሯቸው … እንዴት ዱሽ ማድረግ ማፅዳት እንዳለባቸው የማያውቁ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ … እና በዛን ጊዜ … ስሜቴ ጠፍቷል ብሎ .. የዛኛውን ሰው ስሜት ከመጉዳት እንዴት መስተካከል እንዳለበት ቢነጋገሩ መልካም ነው፡፡

ቤን፡   በጣም ትክክል … ግን እሱ መጀመሪያ ስትነጋገር ይመስለኛል፡፡ ቦቼ የጠየቀው የመሰለኝ … ይህን ሁሉ አልፈው ሴክስ እያደረጉ እያለ …መሃል ላይ ይኼ ነገር ቢያጋጥም እና ቦተም የሆነው እንደዛው ሴክሱን መቀጠል ከፈለገስ? ነው አይደል?

ቦቼ፡  ሃሃ…. አዎ!

ቤን፡   ተነስተህ ራስህን አፅዳ (ቢች)!!!

ቦቼ፡   እኮ! ሃሃሃሃ

ዳኒ፡   በተጨማሪም አሁን ቦቼ ያነሳው ጉዳይ ለእኔ … አካላዊ ብቻ አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜም ደስ ብሎህ እያደረከው .. የሆነ ሰዓት ላይ ስሜትህ ሊጠፋ ይችላል … እና ማቆም ትፈልጋለህ፡፡ ምንም ነገር ወደስሜትህ ላይመልስህ ይችላል ፤ አብሮህ ያለው ሰው የፈለገውን ነገር ቢያደርግ … አንተ ምንም ዓይነት መልስ ላይኖርህ ይችላል … በቃ…እዛጋር ማቆም ፈልገሃል፤ እና ለኔ… It’s all about respect! አንድ ሰው ማቆም ከፈለገ … ያንን ስሜት ልታከብርለት ይገባል፡፡

ቤን፡   ከዛ ወደ መታጠቢያ ቤት ሄደህ …. ቀዝቃዛ ውሃ ፊትህ እና እንትንህ ላይ ውሃ … ች..ልስ!!!

ዳኒ፡   ሃሃሃ… እኮ!  … ራስህን አቀዝቅዝ (ቢች)!!! … ይገባኛል … ፌር ላይሆን ይችል ይሆናል … ስሜት ምናምን ስለሆነ ማለት ነው፡፡  አንድ ነገር ማወቅ ያለብን ግን … ለዛች ለ2 ደቂቃ ነገር ብለን … የሆነ ሰው ልናጣ እንችላለን፡፡ በመሃልም ቢቋረጥም … ከሴክሱ ይልቅ ሰውነትን … አብሮን ያለውን ሰው ማክበር አለብን፡፡ One night stand ወይም ለአንድ ጊዜ ሴክስ ብቻ የተገናኘህ ቢሆንም … ያ ሰው ስለተስማማ እና አብሮህ ስላለ ነው ያንን ነገር እያደረግህ የነበረው፡፡ ስሜትህንም ያነሳሳው ያ ሰው ነው … ፈቃድ ምናምን እያልን ስናወራ ነገሩን ውስብስብ አደረግነው እንጂ … በቀላሉ አብሮን ለሚሆነው ሰው ክብር ይኑረን ነው ነገሩ፡፡

ቤን፡   የጀርባ ሙዚቃችንስ … ሃሃሃ ( ድድ ድዱን … ድድ ድዱን … የሚለው የማሲንቆ ጨዋታ ላይ ደርሰናል … ዘፈኑ እስኪያልቅ ድረስ ኮረንቲአችንን እየጠጣን ወሬአችንን አቋርጠን አብረን ስንዘፍን ነበር፤ ቦቼ ግጥሙን እንደ ስሙ ነው የሚያውቀው… ሃሃሃ)

ቤን፡  ለማንኛውም … እስቲ ሌላ ነገር ልጠይቃችሁ፡፡ ሦስታችሁንም … አሁን አሁን በአንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች … በተለይም ቴሌግራም አካባቢ … አጫጭር የሆኑ የሀበሻ የወሲብ ፊልሞች እያየን ነው፡፡ በተለይ ዜጋው የሚያውቀው ዕውነታ ነው …. እስቲ ስለዚህ ምን ትላላችሁ? እያየን ስላለነው ለውጥ ምን ታስባላችሁ? ስለዚህ ጉዳይ ፣ ስለ ሴክስ ገበያ … እና ሌሎችም … ሃሳቦቻችሁን እስቲ …

ቦቼ፡   እኔ …በግሌ … ሙሉ በሙሉ እደግፈዋለሁ … ማለት እችላለሁ መሰለኝ፡፡ የደህንነቱ ጉዳይ ብቻ ነው የሚያሳስበኝ፡፡ እንጂ… እ … ራስን በቪዲዮ መቅረፅ በራሱ አንድ ፌቲሽ ነው (ለየት ያለ የሴክስ ተጨማሪ ፍላጎት)፡፡ የራስን ሴክስ በቪዲዮ መቅረፅ ምንም ማለት አይደለም፡፡ የተለመደ ነገር ነው፡፡ እኔ ችግሬ … ደህንነቱ ላይ ነው፡፡ ያ ቪዲዮ ማን ጋር ይደርሳል? ፣ የዛ ሰው ማንነት በደንብ ተደብቋል ወይ? ምን ያህል ተጋልጣል? – ሰውነት ላይ ያለ ንቅሳት ሊሆን ይችላል ፣ ጠባሳ ሊሆን ይችላል ፣ የፀጉር አሰራር አይነት ፣ የሚታወቅ ቀለበት …ሰዓት … የቤቱ ውስጥ ሁኔታ ፣ አቀማመጥ … እነዚህ እነዚህ ነገሮች በደንብ ተደብቀዋል ወይ? የሚለው ነገር ሊታሰብበት ይገባል፤ እና… እነዚህን ቪዲዮዎች የሚሰሩ ሰዎች … ብዙ ነገሮችን ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እነሱ ሊታወቁበት የሚችሉ ልዩ የሆነ ነገር ካለ … ወይም ልዩ ይሆናል ብለው የሚያስቡት ነገር ካለ ባያካትቱት መልካም ነው፡፡ እንዳልኩት … ከደህንነት አንፃር ነው እንጂ መቆጠቤ….

ቤን፡   እንጂ … ዛሬም ባይሆን … ነገ የሚቀር ነገር አይደለም፡፡

ቦቼ፡   አዎ! አሁን ማነው ፖርን የሚያይ … የኢትዮጵያ ፖርን ብሎ የማይፈልገው? ወይም ፈልጎ የማያውቀው? እና … ያንን መወንጀል .. ለኔ… እኔንጃ … የ Hipocrisy … ወይም ግብዝነት ሌላው መንገድ ነው፡፡

ዳኒ፡   Thank you! እኔ እንዲያውም … ሰዎች ያን ያህል በፆታዊ ተማርኮአቸው ነፃ መሆናቸው ያስደስተኛል፡፡ እዛ ደረጃ ለመድረስ ብዙ ድፍረት እና ወኔ ይጠይቃል፡፡ አብዛኞቻችን እንዲያውም ሰው ለማግኘት በምንቸገርበት ጊዜ ላይ እንደዚህ በራሳቸው ተማምነው ቪዲዮ የመቅረፅ ደረጃ ላይ የደረሱ ሰዎች መኖራቸው በራሱ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ቦቼ ካለው ከደህንነቱ ጉዳይ በተጨማሪ እኔን የሚያሳስበኝ ነገር ምንድን ነው … ሰዎች እየሰሩ ያሉትን ነገር በደንብ ያውቃሉ ወይ? ሙሉ በሙሉ ስለሚሰሩት ነገር ፣ ኋላ ላይ የሚመጣውን ውጤት (ደግም ሆነ ክፉ) በደንብ ተረድተውታል ወይ? … በተመሳሳይ ደግሞ … በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ፣ በሙሉም ይሁን በከፊል ኮሚኒቲውን ይወክሉታል፡፡ እና ምን እያደረጉ እንደሆነ በደንብ ከተረዱ እና ጥንቃቄን ከጨመሩበት ….

እንደገና ደግሞ የሴክስ ሥራ … ሥራ ነው፡፡ ነገር ግን ልክ እንደ ሌሎች ስራዎች አክብረውት … የራሳቸውንም የሌላውንም ደህንነት እየጠበቁ … ይሥሩ ነው የምለው፡፡  በሥነስርዓት ይስሩት … የሚጠይቁትን ይቀበሉ ፣ ያልተገባቸውን አይውሰዱ፡፡ ፍትሃዊ ግብይት ይሁን … ሃሃሃ ፡፡ እና … ምን መስራት እንደሚፈልጉ ካወቁ … ሥራ ብለው አምነውበት ከያዙት… ይስሩ፡፡

ቦቼ፡   እ… ሰዎች በገዛ ሰውነታቸው የፈለጉትን ነገር ለማድረግ ምንም ዓይነት ምክንያት ፣ ለማንም ማቅረብ አይጠበቅባቸውም፡፡ የምትፈልገውን ነገር ማወቅ ማለት … በጣም ትልቅ መገለጥ ነው …ትልቅ መገንዘብ ነው፡፡ ወደ ቪዲዮው ስመለስ … ቅፅበታዊ ውሳኔ ሊሆን ይችላልና … ኃላ ላይ የሚወጣውን ነገር ከግምት ውስጥ ያላስገባ እንዳይሆን መጠንቀቅ አለብን፡፡

ዳኒ፡   በትክክል! ቅፅበታዊ ስላልከው ነገር … በዛች ቅፅበት የሚሰማህ ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን .. በዛች ሰባራ ሴኮንድ የምታደርጋት ነገር ቀሪው ህይወትህን የምታበላሽ እንዳትሆን ሙሉ ጥንቃቄን ማድረግ ነው፡፡ ለዛም ነው … ማንኛውንም ነገር ስናደርግ … እነዛን ነገሮች የምር ፈልገናቸው ነወይ? ለምን እንደምናደርጋቸው ተረድተን ነወይ?  … አውቃለሁ ስሜታዊ ሆነን ነው የምናደርጋቸው … ነገር ግን ብዙ ነገር የምናጣበት ነገር መሆን የለበትም፡፡ ስለዚህ … ቅድም ያልከው የደህንነት ሁኔታን ማወቅ የሚመጣው … ነገሮችን ትኩረት ስትሰጣቸው ነው፡፡

አሁን ያሉት ግን… አንዳንድ ቪዲዮዎች ልጆቹ ፊታቸው እስኪታይ ድረስ የተቀረፁ አሉ፡፡ እነዚህ ቪዲዮዎቸ ለግል ፍላጎት ብቻ የተሰሩ ቢሆኑ እነዚህ ሚዲያዎች ላይ የሚወጡ አይመስለኝም … ለዚህ .. ለሰው እይታ ታስበውም ከሆነ … የተጠቀሱትን ነገሮች ከግምት በማስገባት ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡

ቤን፡  ሁለታችሁም ያነሳችኋቸው ሃሳቦች ደስ ብለውኛል፡፡ የምትፈልገውን ነገር ለይተህ ስታውቅ እኮ እንዲያውም … እነዚህ ነገሮች ያስፈልጉኛል … እነዚህን ነገሮች ማየት አለብኝ እያልክ ማስታወስ አይጠበቅብህም፡፡ ሁልጊዜ ዝግጁ ትሆናለህ፡፡ ኮንዶሙም ፣ ማለስለሻውም ፣ ሌላውም የደህንነት መጠበቂያ መንገዶችህ … ቀድመህ መዘጋጀት ያለብህ ነገሮች በሙሉ አዕምሮህ ውስጥ ስለሚኖሩ … እንደ ክለሳ ነው የምታያቸው እንጂ፤ በስሜት ተገፋፍተህ የገባህበት ነገር ግን … ሁልጊዜ “ኡ! ይኼን ነገር ረስቼ! “ … “ወይኔ ያንን ነገር ሳላደርግ” በሚሉ ድንግሮች እና ቁጭቶች ይሞላል፡፡

እናንተ!!!…. አይበቃንም!? ሰዓቱን ፈጀነው እኮ!

ቦቼ፡  አንድ ነገር ልጨምር … ምናልባት ስትጀምሩ አብሬአችሁ ስላልነበርኩ አውርታችሁበት ከሆነ እኔንጃ … ግን… ስለ ሴክስ አይነቶች …. ሳይበር ሴክስን እንዴት ታዩታላችሁ?  በቴክስት … በቻት … በቪዲዮ ጥሪ… ሊሆን ይችላል… እነዛን ምን እንላቸዋለን?

ዳኒ፡   ሴክስን ሴክስ የሚያስብለው ባህሪው ወይም Activity ምንድን ነው?  የተቀመጠ የነገሮች አካሄድ ፣ ወይም ቅድመ ሁኔታ ፣ ወይም ውጤት … አለ? የሆነን እንቅስቃሴ ሴክስ ለማለት?

ቦቼ፡   እኔንጃ … ያለ አይመስለኝም፡፡ ስለሳይበር ሴክስ ካወራን … አሁን ለምሳሌ ሁለት ሰዎች ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብለው በቻት እያወሩ ስሜቶቻቸውን የሚወጡ ከሆነ … ለኔ እንደ ሴክስ ነው የምቆጥረው፡፡ አካላዊ ንክኪ ባይኖራቸውም  ሃሳቡን ግን በአዕምሮአቸውም ቢሆን እየተገበሩት ስለሆነ ማለት ነው፡፡ ሴክስ…አዕምሮ ውስጥ ያለ ሃሳብ ስለሆነ፡፡ እና በቴክስት… በቻት የሚደረግ ሴክስ … የተለመደ ነው፡፡

ዳኒ፡  በተለይም አሁን በደንብ መለመድ አለበት፡፡

ዊሊ፡  ኮሮና ቫይረስ!!!!  ሃሃሃሃሃሃ

ቦቼ፡   ሃሃሃሃ…. እና.. ሳይበር ሴክስ… የመጨረሻ ግብ ላይኖረው ይችላል፤ ወይም የመጨረሻው ግብ መርጨት ላይሆን ይችላል፤ እና…. ሴክስ … ሀሳብ ነው፡፡

ቤን፡   እሺ…. ለማንኛውም … ሰክረን እዚሁ ስንለፈልፍ ከማደራችን በፊት በዚሁ እንቋጨው! እንግዶቼ ሆናችሁ ስላወራችሁኝ ….. አልልም! ስኳሬን ጨርሳችሁታል! እያንዳንድሽ የስኳር ቁጭ እያደረግሽ ነው የምትወጪው!

ከእያንዳንዳችሁ ጋር ወደፊት በሌሎች ርዕሶች ላይ እንደምንቀድ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡