የኢትዮጵያ ህግ ስለ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ምን ይላል?

የኢትዮጵያ የወንጀልኛ መቅጫ ህግ ስለ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ምን ይላል?

ሁላችንም እንደምናውቀው የተመሳሳይ ፆታ ፍቅር ወይም ግንኙነት በኢትዮጵያ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 629/30 መሠረት እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስራት የሚያስቀጣ ተግባር ነው፡፡

ዛሬ ህጉ ይቀየር ወይም ይሻሻል ፣ ወይም ደግሞ ህጉ ትክክል አይደለም የሚል የመከራከሪያ ሀሳብ አይደለም ይዤ የመጣሁላችሁ፡፡ መጀመሪያ ህጉ በቀላሉ ምን ይላል? የሚለውን አንዳንድ ጥቆማዎች ላካፍላችሁ እንጂ፡፡

በ2004 (እ.ኤ.አ) የተሻሻለው እና አሁን የምንገለገልበት “ለተፈጥሮ ባህርይ ተቃራኒ የሆኑ…” በሚል ሃሳብ ላይ የተመሰረተው የኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 629 ፡

“ማንም ሰው ከእርሱ ጋር አንድ ዓይነት ፆ ካለው ከሌላ ሰው ጋር ግብረሶዶም ወይም ለንፅህና ክብር ወይ ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነውን ሌላ ድርጊት የፈፀመ እንደሆነ፤

በቀላል እሥራት ይቀጣል፡፡”

ይላል፡፡ (ከስያሜው “ግብረሶዶም” ጀምሮ (ይኼን ቃል ስጠላው ብታዩ) ስህተት ባገኝበትም… ለዛሬ ይለፈኝ)

ወረድ ብሎም በአንቀፅ 630 ላይ ወንጀሉን የሚያከብዱ ጠቅላላ ሁኔታዎችን ይዘረዝራል፡፡ ልብ በሉ ‘የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ መሆን’ አላለም ፤ ‘…ድርጊት የፈፀመ እንደሆነ’ አለ እንጂ፡፡

ከአንቀፅ 630 እስከ 632 ደግሞ ይህንን ወንጀል የሚያከብዱ የተለያዩ ሁኔታዎችን እየዘረዘረ የቅጣት እሥራቱ እስከ 15 ዓመት ድረስ ያደርሰዋል፡፡ ህጉ የዕድሜ ሁኔታዎችን እና ሌሎች ከዚህ በታች ባሉ ምስሎች ላይ የተጠቀሱ ሁኔታዎችን መሠረት በማድረግ እስከ ዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ሊያድግ ይችላል፡፡


የኢትዮጵያ የወንጀልኛ መቅጫ ህግ ፡ አንቀፅ 629/630
የኢትዮጵያ የወንጀልኛ መቅጫ ህግ ፡ አንቀፅ 630
የኢትዮጵያ የወንጀልኛ መቅጫ ህግ ፡ አንቀፅ 631
የኢትዮጵያ የወንጀልኛ መቅጫ ህግ ፡ አንቀፅ 631
የኢትዮጵያ የወንጀልኛ መቅጫ ህግ ፡ አንቀፅ 631

ምንም እንኳን ሌሎች ብዙ ፣ ሁሉንም ሰው በእኩል ደረጃ ሰብዓዊ መብቱን የሚያጎናፅፉ ፣ ግላዊነትን እና ጥበቃን ጨምሮ ፣ አንቀፆች  በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት ውስጥ ቢኖሩም እነዚህ መብቶች እና ጥበቃዎች ግን በአፈፃፀም ደረጃ ለኢትዮጵያ ተመሳሳይ ፆታ አፍቃርያንም ሲያገለግሉ አይስተዋልም፡፡

ቸር ያውለን!

© የዜግነት ክብር – ከዶሚነስ ጋር 2012 ዓ.ም

ምንጭ፡ የኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ