Habesha
ሻይ ኮረንቲ – ክፍል ሁለት
እናንተ? ሁለተኛውን ክፍል አዘገየሁባችሁ አይደል? ምን ታመጣላችሁ!!!! የምር ስወዛገብ ነበር … በሀሳብ! ይኼ ኮሮና እኮ…. እናላችሁ … “በዚህ በጭንቅ ጊዜ አሁን እነዚህ ሦስት ሰዎች ስለ ወሲብ ሲያወሩ ማን መስማት ይፈልጋል?” በሚል ፍርሃት እና “ ሁሉ ነው ስለ ኮሮና የሚያወራው … እንዲያውም አዕምሮን ትንሽ ከዛ ጭንቅ ለተወሰኑ ደቂቃዎችም ቢሆን ፈታ የሚያደርግ ነገር ብናነብ?” በሚል መሟገቻ ስወዛገብ
ሻይ ኮረንቲ – ክፍል አንድ
ከዳኒ ስኮት ፣ ዊሊ ብሮ እና ቦቼ ቢኖ ጋር የዛሬው እንግዳዬ ዳኒ ስኮት ነው፡፡ …. ነበር! ዊሊ ብሮ ተቀላቀለን ፣ ኋላ ላይም ቦቼ ቢኖ ቦንቦሊኖ ይዞ ከች አለ! ያው ዘመኑ የበሽታ ሆኗልና ከቤት ከትመናል፡፡ የምሽቱን ነፋስ ለመከላከል ሻይ ኮረንቲ ፉት እያልን ፣ እየቀደድን ሳለ … ወሬአችን ላይ ትንሽ ቁምነገር ባይ ጊዜ … ለምን ለናንተ አላጋራችሁም
ሰውነት
ሰው ነሽ! ሰው ነህ! ሰው ነኝ! ሰው ናት! ሰው ነው! ሰው ናቸው! ሰው ነን! ሰው ናችሁ! …. አስተውላችሁ ከሆነ በዚች አጭር ፣ ነገር ግን ብዙ ፅሁፍ ውስጥ …. ነህ ፣ ነሽ ፣ ነን፣ ናችሁ… ሌሎችም፤ በሚባሉ የመለያ እና የመለያ (ሲጠብቅም ሲላላም) ብዝሃነት ውስጥ አንድ ነገር ብቻ ተደጋግሟል – ሰው! ሰውነት ጥርስ ካላበቀለው ፣ የሌላ አዋቂ
ቶና – ከድንቡሼ ጋር
ሰላም ሰላም ቤተሰብ! እንዴት ከርማችኋል!? የዚህ ቅዳሜ እንግዳዬ ድንቡሼ ገላ ወይም በቀድሞ ስሙ ስክሮል ዜር ይባላል፡፡ ለአብዛኛው የፌስቡክ ዜጋ ተጫዋች ፣ ቀልደኛ እና ተግባቢ ነው፡፡ ለአንዳንዶች ደሞ …. ስለዚሁ ግልፅ እና ተጫዋች ባህሪው ፣ ነገሮችን ስለሚያይበት መንገዶች ፣ ስለ ህይወት ገጠመኞቹ ፣ ያለ ፈቃድ ስለመጋለጥ … ራሱን የተቀበለበት ሂደት … ስለ ቤተሰብ … ሌላም ሌላም
አቦል ቡና – ከናቲ ጋር
ጥያቄ፡ በመጀመሪያ የቡና ግብዣዬን ስለተቀበልከኝ እና ልታወራኝ ስለፈቀድክ ፣ እንዲሁም የመጀመሪያ እንግዳዬ በመሆን መሞከሪያዬ በመሆንህ …. እጅግ ላመሰግንህ እወዳለሁ፡፡ ናቲ፡ ሃሃ…. እኔም ስለጋበዝከኝ አመሰግናለሁ፡፡ ጥያቄ፡ እንዴት ነበር የጀመርከው? ናቲ፡ ምን…ዜግነት? ሃሃ ጥያቄ፡ እ? እንዴት ነበር የመጀመሪያ ጊዜህ? ናቲ፡ የመጀመሪያ ጊዜ ሰው ያገኘሁት ከ12 ዓመት በፊት ነበር፡፡ ግቢ ነበርኩ፡፡ ከዛ ረፍት ላይ ከሀገር ውጭ የመሄድ አጋጣሚ ገጥሞኝ ነበር፡፡ እዛ ነው የመጀመሪያ ሀበሻ