ከዳኒ ስኮት ፣ ዊሊ ብሮ እና ቦቼ ቢኖ ጋር
የዛሬው እንግዳዬ ዳኒ ስኮት ነው፡፡ …. ነበር! ዊሊ ብሮ ተቀላቀለን ፣ ኋላ ላይም ቦቼ ቢኖ ቦንቦሊኖ ይዞ ከች አለ!
ያው ዘመኑ የበሽታ ሆኗልና ከቤት ከትመናል፡፡ የምሽቱን ነፋስ ለመከላከል ሻይ ኮረንቲ ፉት እያልን ፣ እየቀደድን ሳለ … ወሬአችን ላይ ትንሽ ቁምነገር ባይ ጊዜ … ለምን ለናንተ አላጋራችሁም ብዬ አሰብኩ፡፡
ወሬአችን ሙሉ ለሙሉ በየግላችን ያለንን ግላዊ አመለካከቶች ማዕከል ያደረገ ፣እንዲዉም ከግላዊ ልምዶቻችን በመነሳት የተወያየንበት ስለሆነ ትኩረቱ የወንድ ዜጎች የወሲብ ሕይወት ላይ ነው፡፡ አራታችንም … ከዛ ግሩፕ የመጣን ነንና፡፡
በተረፈ … እቤታችሁ እንደሆናችሁ አምነን ፣ ሻይ ኮረንቲ ተጋበዙልን እና … ፉት እያላችሁ ቀደዳችንን ታዘቡልን፡፡ አስተያየቶቻችሁንም ንገሩን፡፡ ወሬአችን የሙሉ ቀን ነበረና በዚህ አያልቅም … ይህን ከወደዳችሁት … ቀሪውን ቶሎ አጋራችኋለሁ፡፡ ይመቻችሁ!
እጆቻችሁን መታጠብ እንዳትረሱ!
ቤን፡ በመጀመሪያ ልታወራኝ ስለተስማማህ በጣም አመሰግናለሁ፡፡
ዳኒ፡ ሃሃሃ…. በግድ ገፍተኸኝ እኮ ነው
ቤን፡ ካልፈለግህ መቅረት ይችላል፡፡
ዳኒ፡ እንዳትቀርፀኝ ምናምን እንጂ… ችግር የለውም፡፡ ይኼ የኛ የቴክኖሎጂ ዘመን ያስፈራኛል፡፡
ቤን፡ ያው እንግዲህ… የሚስማማንን እየወሰድን ፣ የማንፈልገውን ነገር ደግሞ እያስወገድን መቀጠሉ ይሻላል እንጂ … ከቴክኖሎጂ እንኳን ማምለጥ የምንችል አይመስለኝም፡፡
ዳኒ፡ ልክ ነው
ቤን፡ እና ዛሬ ስለምን ነበር የምናወራው?
ዳኒ፡ ሃሃሃ…. ራስህ ልጠይቅህ ብለኸኝ?
ቤን፡ እሺ… ስለ ሪሌሽንሺፕ ነው አይደል?
ዳኒ፡ ስለ ሴክስ
ቤን፡ ትወደዋለህ መቼም እሱን ነገር….
ዊሊ፡ የማይወደው ማን አለ! ሃሃሃሃ
ዳኒ፡ አሴክሹዋል ሰዎች፡፡ ምንም የሴክስ ፍላጎት የሌላቸው ፣ ከአንድም ሆነ ከዛ በላይ ሰው ጋር ግን በፍቅር አብረው መኖርን የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች አሉ እኮ፡፡
ቤን፡ ልክ ነው፡፡
ዳኒ፡ ፖርን ሀብ የተለቀቀ ቀን በጥቂት ሰዓታት ውስጥ 5 ሚሊዮን ተከታዮችን እንዳፈራ ታውቃላችሁ? ፌስቡክ እንኳን ያን ያህል ተከታይ አልነበረውም መጀመሪያ ላይ፡፡
ዊሊ፡ ይኼን ይኼንማ በደንብ ታውቃለህ፡፡ ሃሃሃ
ዳኒ፡ እንዴ…. ሴክስ እኮ ልክ እንደ መብላት እና መተኛት ምናምን አብዛኛው ሰው ያለው ፍላጎት… ወይም ደግሞ ስሜት ነው፡፡ It’s just another urge. ሁላችንም እኮ ስለ ሴክስ በጣም እናስባለን፡፡ እንደገና ደግሞ ቅርፅ እንሰጠዋለን ፣ መመሪያ እናበጅለታለን… ሴክስ እንዲህ ነው ፣ ሴክስ እንዲያ ነው እያልን እንመዳድበዋለን፡፡ በአፈፃፀሙ ሁኔታ እንገድበዋለን እነጂ … ሴክስ ሀሳብ ነው… በተግባር የሚገለጥ ሀሳብ፡፡
ቤን፡ እሺ…. ሴክስ ላንተ ምንድን ነው?
ዳኒ፡ ሴክስ ለእያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ ትርጉም እንዳለው ይሰማኛል፡፡ It’s subjective. እያንዳንዱ ሰው ከሚያደርገው ፣ ከሚፈልገው እና ከሚመኘው ነገር አንፃር ነው ትርጓሜ የሚሰጠው፡፡
ዊሊ፡ ሰዎች ስንባል ግራ የገባን ነን እኮ፡፡ ሴክስ እንዲህ ነው መደረግ ያለበት ፣ ይኼን ስታደርግ ሴክስ አድርገሃል ማለት ነው… ምናምን እያልን መደብ የምናወጣለት ነገር ትንሽ ግር ያሰኘኛል፡፡
ዳኒ፡ ችግሩ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? በእኔ አመለካከት ሴክስን ስናውቀው (በተለይ እኛ ማህበረሰብ ውስጥ) ለመራቢያነት ብቻ ነው፡፡ በዛም ምክንያት ወዲያው ሴክስን ከመራቢያ አካላት ጋር እናያይዘዋለን፡፡ ከዚያ በመራቢያ አካላት የሚደረግ ግንኙነትን ወይም ወሲብን ብቻ ሴክስ እንለዋለን፡፡
ቤን፡ ታዲያ ሴክስ የምንለው ነገር ምንን ያጠቃልላል ትላለህ?
ዳኒ፡ ብዙ ነገር አለ፡፡ ለምሳሌ የሆነ ጊዜ አንዲት የስነተዋልዶ ጤና ባለሞያ ስለ ሴክስ ስታስረዳ የሰማሁትን ልንገራችሁ፡፡ የሰውን የሰውነት አካላት በሁለት ረድፍ አስቀምጣቸው ሴክስ ነው ብለን የምናምነውን ግንኙነት ልክ እንደ አዛምድ እያዛመደች ስትጠይቀን ነበር፡፡ አብዛኞቻችን ቅድም እንዳልኩት ከቁላ ፣ እምስ እና ፊንጢጣ የዘለሉትን ሴክስ ናቸው ብለን Consider አላደረግናቸውም ነበር፡፡ አፍ ከአፍ ጋር ፣ አፍ ከቁላ ጋር ፣ አፍ ከእምስ ጋር ፣ ቁላ ከእምስ ፣ ቁላ ከፊንጢጣ ፣ ፊንጢጣ ከአፍ ፣ እምስ ከእምስ ….
ዊሊ፡ አንተ!!! ምነው በጥሬ ስማቸው ጠራኃቸው!
ቤን፡ እንዲህ እያልን ነው ነገሩን ሁሉ ሽፍንፍን ድብቅብቅ አድርገን ትውልድ እያጣን ያለነው ባክህ፡፡ በግልፅ መወራት አለበት፡፡ የተፈጥሮአችን አንዱ ክፍል ፣ ያውም ሁልጊዜ የምናሰላስለው ፣ የምናየው ፣ አደገ ፣ አነሰ፣ ሰፋ ጠበበ ምናምን እያልን ትኩረት የምንሰጠው እስከሆነ ድረስ በተሰጣቸው ስም ብንጠራቸው ምን አለበት፡፡
ዳኒ፡ ተመሰልህ? ሃሃሃ
ዊሊ፡ እሺ ቀጥልልን
ዳኒ፡ እና ብዙ አይነት ግንኙነቶች አሉ፡፡ እኔ በግሌ ሴክስ የምለው ፣ ስሜቴን… ወይም ያንን የወሲብ ፍላጎቴን የሚያስታግስልኝ ማንኛውም አይነት ነገር… መሳሳም ሊሆን ይችላል ፣ መተቃቀፍ ፣ መተሻሸት ፣ መላፋት … ሌላም ሌላም… ለኔ ሴክስ ነው፡፡ ግዴታ መግባት እና መውጣት የለብንም፡፡
ቤን፡ መቼ ነበር ለመጨረሻ ጊዜ ሴክስ ያደረከው?
ዳኒ፡ ቆየሁ
ዊሊ፡ ለምን?
ዳኒ፡ በጣም ቢዚ ሆኜ ነበር፡፡ ከእናነተ ጋር፡፡ ሃሃሃሃሃሃ
(ሳቅ በሳቅ)
ዳኒ፡ የምሬን እኮ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ከሰው ጋር ለዴት እቀጣጠርና … የቅርብ ጓደኞቼ ሲደውሉልኝ ምናምን ከነሱ ጋር የማሳልፈው ጊዜ ያጓጓኝና … እሰርዘዋለሁ፡፡
ቤን፡ ኧረ ልክ ነህ! ሃሃሃ
ዳኒ፡ በፊት በፊት ቤት ቁጭ ብዬ… ሲደወልልኝ ወዲያው ነበር ብድግ ብዬ የምወጣው፡፡ ለሴክስም ሆነ ለቡና ምናምን
ዊሊ፡ ዱሽ (ከወሲብ በፊት ፊንጢጣን የማፅዳት ስነስርዓት) ምናምን ሳታደርግ? ቶፕ ነኝ እያልክ ነው?
ዳኒ፡ ይቅርታህንና….እኔ በሮል አላምንም፡፡ ሰው ሁሉ የሚያስደስተውን ያድርግ፡፡ መጨረሻው ስሜትን መመገብ ፣ መደሰት አይደለ? “እኔ ይኼን ብቻ ነው የማደርገው” … “እንትና ቶፕ ወይም ቦተም ነው” የሚል ነገር ብዙም አይደላኝም፡፡ ቅድም ያልኩት የሴክስ የተገደበ እሳቤ ነው እነዚህን ስያሜዎች ያመጣቸው እንጂ፡፡ እርግጥ ነው የሰው ፍላጎት ይለያያል፡፡
ቤን፡ እንዴት ነበር የመጀመሪያ ጊዜ የሴክስ አጋጣሚህ?
ዳኒ፡ መጀመሪያ ላይ በጣም ያስፈራ ነበር፡፡ በባህሪዬ የሆነ ነገር ማወቅ ከፈለኩ ስለዛ ነገር የበለጠ ለማወቅ እሞክራለሁ፡፡ እናም በጣም ከማሰላሰሌ የተነሳ አንዳንዴ የማስባቸው ሃሳቦች ያስደነግጡኝ ነበር፡፡
ዊሊ፡ ጥያቄው ስለመጀመሪያ ጊዜ የሴክስ አጋጣሚህ ነበር
ዳኒ፡ ሃሃሃሃሃ…. ያን ያህል ብዙም አላስታውሰውም፡፡ ከወንድ ጋር የመጀመሪያዬ ነበርና ደንግጬ ነበር፡፡
ዊሊ፡ ከሴት (ተቃራኒ ፆታ) ጋር ግንኙነት ነበረህ ማለት ነው?
ዳኒ፡ አንድ ጊዜ አዎ፡፡ አጋጣሚው ትንሽ ያስቅም ያሳዝንም ነበር፡፡ እንግዳ ነገር ነበር ለኔ፡፡
ቤን፡ እንዴት?
ዳኒ፡ ምክንያቱም ከፍቅረኛዬ ጋር ሳይሆን ከሌላ ሴት ጋር ነበር ያደረግሁት፡፡ ሃሃሃ
ቤን፡ አንተ ወስላታ!!!
ዳኒ፡ ሃሃሃ… እንደዛ አይደለም፡፡ ስለወደድኳት ነበር የወሰለትኩባት፡፡
ዊሊ፡ እንዴ… ምን ማለት ነው?
ዳኒ፡ ልጅቷን በጣም ነበር የምወዳት፡፡ እንዳልኳችሁ… ስለ አንድ ነገር ማወቅ ከፈለኩ እስከ ጥግ ድረስ እሄዳለሁ፡፡ ሴክስ ደግሞ ያኔ በጣም ትልቅ ነገር ነበር፡፡ እና ከሷ ጋር ሴክስ ከማድረጌ በፊት እና የማላውቀው ነገር ላይ ተንጠልጥዬ እንዳላስከፋት ወይም እንዳላስደብራት…. ምክንያቱም በወቅቱ ሴክስን እንደ ትልቅ ነገር ነበር የምናየው… ከዛ በኋላ ያለው ግንኙነታችን በሴክስ ምክንያት እንዲበላሽ ስላልፈለኩ…. ከሌላ ሰው ጋር መሞከር እንደነበረብኝ ወሰንኩ – ከዛ ለሷ የተሻለ ሴክስ ለመስጠት፡፡
ዊሊ፡ ምን ጉድ ነህ?
ዳኒ፡ የምሬን እኮ ነው! ምክንያቴ እሱ ብቻ ነበር፡፡ የሚጠብቀኝን ነገር በደንብ አውቄ ልገባበት ነበር የፈለኩት፡፡ ነገሮችን ካልተቆጣጠርኩ አልችልም፡፡ በተለይ ከወደደኩት ሰው ጋር ከሆነ…. ሰዎቸን ሳይሆን ሁኔታዎችን እየተቆጣጠርኩ… ነገሮችን ግን ቀድሜ እያወቅሁ… ያንን ሰው አስደስቼ እኔም መደሰት ነው የምፈልገው፡፡
ዊሊ፡ እሷስ የመጀመሪያዋ ነበር?
ዳኒ፡ አልነበረም፡፡ ሌሎች የወሲብ ጓደኞች ነበሯት፡፡
ቤን፡ ሃሃሃሃሃሃ…. እና ከዛ ምን ተሰማህ?
ዳኒ፡ ከሴት ጋር ወሲብ መፈፀም እወዳለሁ ማለት አልችልም፡፡ የኔ ችግር ምን መሰላችሁ…. እምስ አልወድም ፣ ቁላ አልወድም ፣ ቂጥ አልወድም…. ለእነዚህ የአካል ክፍሎች የተለየ ፍቅር ወይም ሰፍ የሚያስደርግ ነገር የለኝም ፤ ያን ያህል የወሲብ ስሜቴንም አይቀሰቅሱትም፡፡ የማገኘው ሰው ሰዋዊ ሁኔታዎች እና ባህሪው ግን…..
ቤን፡ ስለዚህ ዳኒሴክሹዋል ነህ ማለት ነው?
ዳኒ፡ ሃሃሃ…. I am my own sexuality.
ዊሊ፡ እሺ ከተመሳሳይ ፆታ ጋርስ?
ዳኒ፡ ዌል እንግዲህ…. እንደነገርኩህ ብዙም አላስታውሰውም ነበር፡፡ በጣም ኤክሳይትድ ሆኜ ነበር፡፡ እና… እ….
ቤን፡ ሃሃሃ…. አይዞህ አውራው! We don’t judge you!
ዳኒ፡ እናላችሁ… የመጀመሪያ ጊዜዬ….. ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ የተቀጣጠርኩት ከሆነ ልጅ ጋር ነበር፡፡ ሲመጣ ጓደኛውን ይዞት መጣ….
ቤን፡ የቀጠርኩትን ትቼ ጓደኝዬውን…… ልትለኝ ነው አይደል? (ጉድ ጉድ ጉድ)
ዳኒ፡ ሃሃሃ…. ከተቀጣጠርኩት ጋር ለሴክስ አልተመቻቸንም ነበራ!! እህ! ሁለታችንም የምንፈልገው ነገር የተለያየ ስለነበረ … ምንም እንደማይፈጠር ገብቶን ነበር፡፡ እንደገና ለመጀመሪያ ጊዜ መገናኘታችንም ነበር፡፡ ጓደኛው ግን በቃ… ሃሃሃሃ…. ተግባብተን ፣ ተጣጥመን ነበር ብል ይቀላል መሰለኝ፡፡
ዊሊ፡ እ….ሺ! ከዛስ?
ዳኒ፡ ከዛማ በቃ… ማታ ላይ ወክ እያደረግን … ጭር ብሎ ነበር፡፡ ከዛ መሳሳም ጀመርን … ምናምን….. ከዛ በእጁ……
ቤን፡ ሃሃሃሃሃ…. በቃኝ!!!!
ዳኒ፡ ፔኔትሬቲቭ ሴክስ እኮ አልነበረንም፡፡ የመጀመሪያዬ ስለነበር ግን ….. መጨረሻ ላይ ማልቀስ ጀመርኩ፡፡
ቤን፡ እንዴ! ለምን?
ዳኒ፡ የመጀመሪያዬ ነበራ! ብዙ ነገር ያረጋገጥኩበት አጋጣሚ ነበር፡፡ ያ አጋጣሚ ማለት… ሁልጊዜ የሚሰማኝ ስሜት ትክክል መሆኑን ያረጋገጥኩበት ነበር፡፡ ውዝግቤ መቋጫ ያገኘበት አጋጣሚ ነበር፡፡ የሚገርመው ግን… ቅድም እንዳልኩህ ሴክስ ማለት ፣ በተለይ ከተመሳሳይ ፆታ ጋር የሚደረግ…. በወቅቱ ለእኔ የሆነ ሃሳብ እንጂ በተግባር የሚፈፀም ነገር አይመስለኝም ነበር፡፡ ብልቱን እንኳን መንካት አልቻልኩም ነበር፡፡ ልክ ስጨርስ ግን…. እውነት መሆኑ ሲገባኝ ነበር ማልቀስ የጀመርኩት፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር ደግሞ…. ጠጋ ብሎ እንባዬን ሳመኝ….. በጣም የሚገርም መልካም ልጅ ነበር፡፡
ቤን፡ እሺ! ከዚህ በላይ ያንተን የወሲብ ህይወት የማወቅ ፍላጎቱ ብዙም ያለን አይመስለኝም፡፡
ዳኒ፡ ካንተ ይሻላል መቼም!
ቤን፡ ሃሃሃ
ቤን፡ የሆነው ሆኖ…. እስቲ ስለዜጋው የወሲብ ህይወት አውራኝ … ስለምታውቀው፡፡ ምን ይመስላል? በተለይም ምን ያህል ነፃነት አለው? ከጤናውስ አንፃር ? ከጥቃትስ ደህንነቱ የተረጋገጠ ነወይ? በአንዱ ወይም በሁለቱ ወይም ከዛ በላይ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነው? … እስቲ ያለውን… የታዘብከውን ወይም ግላዊ ዕይታህን እየነገርከን እናውራ እስቲ
ዳኒ፡ እኔ… የማስበው… እንደ ዜጋ ማህበረሰብ …ወሲባዊ ጉዳዮች ላይ ከሌሎች የተሻለ አመለካከት አለን ብዬ አስባለሁ፡፡ በግሌ፡፡ በተሻለ ሁኔታ ለሴክሹዋል ነገሮች ክፍት እና ነፃ ነን፡፡ ብዙ ሰዎች ራሳቸውን ወይም ወሲባዊ ፍላጎቶቻቸውን ይገድቡታል … ማድረግ የሚፈልጓቸው ነገሮች እያሉ ግን ቁጥብ ይሆናሉ፡፡ እኛጋ… ከሞላ ጎደል ይኼ ባህሪ የለንም፡፡ የሚያስደስተንን ነገሮች ለማድረግ ፈቃደኞች እና ደፋሮች ነን፡፡ ያ ነገር መልካም ሆኖ ሳለ… ነገር ግን ለብዙ ችግሮችም ተጋላጭ አድርጎናል፡፡ አሁን ለምሳሌ … ሁሉም የሥነ ተዋልዶ ጤና መረጃዎች የ”ቀጦች ሴክስ” የሚባለውን ማዕከል አድርገው የተዘጋጁ በመሆናቸው ለኛ ለዜጎች የማይሰራ ይመስለናል መሰለኝ – ጥንቃቄ የጎደለው ወሲብ ለመፈፀም ቅርብ ነን፡፡
ዊሊ፡ እንደገናም በፊንጢጣ በኩል የሚደረግ ወሲብ ለኤች አይቪም ሆነ ለሌሎች በሽታዎች ተጋላጭ አያደርግም የሚል ዕምነትም እስካሁን አለ፡፡
ዳኒ፡ እኮ!!! … ኧረ ደሞ… በሽታዎቹን እንኳን ብንተዋቸው … ቶፕ ብቻ ከሆንኩ ጌይ አይደለሁም የሚባልም አስተሳሰብ አለ፡፡ ብዙ ሰዎች አውርቻለሁ .. እንደዛ አይነት አስተሳሰብ ያላቸው፡፡ ማለቴ…. ዕውነት ሊሆን ይችላል፡፡ ወሲባዊ ባህሪይን እና ፆታዊ ተማርኮን ለያይተን ማየታችን ጥሩ ሆኖ ሳለ ፣ ከሱ ጋር ተያይዘው የሚመጡ አፈታሪኮችን ፣ በተለይም ከራስ አልፎ የሌላውን ጤና የሚመለከቱ ጉዳዮችን ግን መለየት መቻል አለብን፡፡ አሁን ለምሳሌ… ወሲባዊ ባህሪይን ስንመለከት፡ ከወንድ ጋር የሚተኛ ወንድ ሁሉ የግድ ዜጋ (ጌይ) ነው ማለት አይደለም፡፡ በፊንጢጣ በኩል የሚደረግ ወሲብ ፣ ከየትኛውም ፆታ ጋር ቢሆን ፣ ማንኛውም ሰው ፣ ቀጥም ሆነ ዜጋ ሊኖረው የሚችል ወሲባዊ ባህሪይ ነው፡፡
ቤን፡ ከጥንቃቄ አንፃርስ? ዜጋው ጥንቃቄው እንዴት ነው? ከብዙ ሰዎች ጋር እንደምታወራ አውቃለሁ እና… ምን ይመስላል?
ዳኒ፡ ግራ የገባው ነው! ሃሃሃሃ…. ብዙ ነገር አለ፡፡ አንዳንዶች ጠንቃቃ ናቸው ፣ አንዳንዶች ደግሞ አይደሉም፤ በተለይ ግን…. መረጃው አላቸው ፣ ያውቃሉ ፣ ጠንቃቃ ለመሆን የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎችን ማግኘት ይችላሉ የምትላቸው ሰዎች ፣ በተለይም በተለይም … ጥንቃቄን ሲያበረታቱ የምታያቸው ሰዎች ከሚያወሩት በጣም የተቃረነ ነገር ሲያደርጉ ታያለህ፡፡ ብዙ ጊዜ አጋጥሞኛል፡፡ እና በጠቅላላው …. ጥንቃቄ የታከለበት የወሲብ ባህሪይ ነው ያለን ብዬ ለማለት እቸገራለሁ፡፡ ይህ ግን ዜጋውን ብቻ የሚመለከት ነገር አይደለም፡፡ አንድ ሰው ጠንቃቃ ቢሆን እንኳን ፣ ፍላጎቱን ፣ ኤክስፔሪየንስ ማድረግ የሚፈልገውን ነገር በፈለገው መጠን እንዳያገኝ የሌሎች አለመጠንቀቅ ይገድብበታል፡፡
ዊሊ፡ አዎ… በተጨማሪም… ቅድም እንዳልከው … ዜጋውን ማዕከል ያደረጉ ፣ ጤናማ ወሲብን ፣ ጥንቃቄ የተሞላበት ግንኙነትን የሚያበረታቱ መረጃዎች ፣ እንደ አዲስ አሊያንስ እና 1ዜጋ ከሚያጋሯቸው በስተቀር ፣ በበቂ ሁኔታ አለመገኘታቸው ፣ ማለስለሻ ፣ ዴንታል ዳም… እና ሌሎችም ማቴሪያሎች እንደ ልብ አለመገኘታቸው እንደ ዋና ችግር ቢነሳም ፣ በተለይም መረጃው ባላቸው እና እነዚህን ነገሮች በቀላሉ ማግኘት በሚችሉት ዘንድም ይህ ጥንቃቄ ችላ መባሉ ትንሽ ያሳስባል፡፡
ቤን፡ ልክ ነህ፡፡ በዚህ በጥንቃቄ ዙሪያ … ብዙ ጊዜ ምን አስባለሁ መሰላችሁ፡፡ እኔ አሁን ያለን መረጃ ሳይኖረኝ በፊት ፣ አሁን ያለኝ በራስ መተማመን ፣ “እኔ እንዲህ ነኝ” ፆታዊ ተማርኮዬን ስም ሰጥቼው ከመቀበሌ በፊት ፣ ወይም ደግሞ አሁን የማውቀውን ጥንቃቄ የተሞላበት ወሲብ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሳላውቅ በፊት ፣ የዜጋውን ማህበረሰብ ከመቀላቀሌ በፊት ፣ ከወንድ ጋር ወሲብ ጀምሬ ቢሆን እንዴት ዓይነት የወሲብ ህይወት ይኖረኝ ነበር? ብዬ ራሴን ስጠይቅ …. አሁን ላይ ጠንቃቃ አይደሉም? ለምን ሎሽን እና ቫዝሊን ይጠቀማሉ? ለምን ካለ ኮንዶም ወሲብ ይፈፅማሉ? እያልኩ የምወቅሳቸውን ሰዎች በንዝህላልነት ነው የሚያደርጉትን የሚያደርጉት ለማለት እቸገራለሁ፡፡ አሁን እየተሰራ ባለው ነገር ላይ በተጨማሪ እነዚህን ሰዎች በሆነ አጋጣሚ ወይም መንገድ ተደራሽ የሚያደርግ ነገር ቢኖር መልካም ነው፡፡
ዳኒ፡ አዎ! እንደገና ደግሞ ምን አለ መሰላችሁ፡ የሆነ አጋጣሚ ልንገራችሁ… አንድ ጊዜ ከሆነ ልጅ ጋር ፣ ገና ሰው መተዋወቅ ፣ ዴት ማድረግ ምናምን የጀመረ ልጅ ነው …. ማውራት ጀመርን፡፡ መጀመሪያ ላይ ትንሽ ተጀናጅነን ነበር፡፡ ሃሃሃሃ…. በነገራችን ላይ ብዙ ሰዎች እንደሚሉት “እድሜ ፣ ሮል…. ምናምን” የሚሉት ጥያቄዎች እኔን አይረብሹኝም፡፡ አብዛኞቻችን አድርገነው ያለፍነው ነገር ነው… በተጨማሪ ደግሞ ለማውራት እና ለመጀናጀን ይህን በሉ ፣ ይህን ጠይቁ… ወይም ይህን አትበሉ ተብሎ የተቀመጠ ህግ የለም፡፡ ካልተመቸህ አለመመለስ ትችላለህ… ፌስቡክን ለመዝናኛነት እና ለአንዳንድ ቁምነገሮች የምንጠቀምበት እንዳለን ሁሉ … ለመጀናጀን የሚጠቀሙበትም እንዳሉ መረዳት አለብን፡፡
ዊሊ፡ እኔም ያኔ ፌስቡክ ስጀምር መጀመሪያ ላይ ከማወራቸው ሰዎች አብዛኞቹ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ነበር የሚጠይቁኝ፡፡ እኔም በቃ… ባህሉ እንደዛ ነው ብዬ ሰዎችን እጠይቅ ነበር፡፡ ኋላ ላይ ግን… ሰዎችን በአካል ማግኘት ስጀምር … ጓደኞቼን ሳገኝ… ነገሮች ሁሉ ስለ ሴክስ እንዳልሆኑ ሲገባኝ ፣ ለሴክስም ቢሆን እነዚህ የሚጠየቁት ጥያቄዎች ለምፈልገው ነገር ብዙም አስተዋፅዖ እንደሌላቸው ስረዳ እየተውኩ መጣሁ እንጂ… የተቀመጠ መመሪያ የለም፡፡
ዳኒ፡ እና ከዛ ልጅ ጋር እያወራን… ዴት ለማግኘት ወይም ለሴክስ ብዬ ፌስቡክ እንደማልጠቀም ነግሬው ተስማማን፡፡ ከዛ ኋላ ላይ ከሌላ ሰው ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ለወሲብ ቀጠሮ እንዳለው እና፣ የቀጠረውን ሰው እንዴት ማስደሰት እንዳለበት አንዳንድ ነገሮችን እንድነግረው ጠየቀኝ፡፡ የመጀመሪያዬ ነው ሲለኝ ወዲያው ለጥንቃቄ ምን እንደሚጠቀም ጠየኩት፡፡ ኮንዶም እንደያዘ ነገረኝ፡፡ ለማለስለሻ ደግሞ ሎሽን ወይም ቫዝሊን ሲሉ እንደሰማ ነገረኝ፡፡ እና መረጃዎች እንዴት ለእነዚህ ለራሳቸውም ለዜጋውም አዲስ የሆኑ ሰዎች መድረስ እንደሚገባቸው እና ብዙ መሰራት እንዳለበት አስባለሁ፡፡ በእነዚህ ማቴሪያሎች ስርጭት ረገድ… አሁን ላይ 1ዜጋ ፣ አዲስ አሊያንስ እና ሌሎች ግለሰቦች እየሰሩ ያሉት ነገር ሊበረታታ ይገባል፡፡ እና ለሰዎች ማስተላለፍ የምፈልገው ነገር ደግሞ ፣ ሁልጊዜ ራሳችንን ፣ ደህንነታችንን እየጠበቅን ያለመጨናነቅ ህይወታችንን በተቻለን መጠን በደስታ ለመምራት መጣር አለብን፡፡ ነገሮችን አለማወቅ አያስወቅስም ፣ እያወቁ ግን ችላ ብሎ ማለፍ አይገባም፡፡ ጤናችን እና ደስታችን የህይወት ስጦታዎቻችን ናቸው፡፡ ከላይ የጠቀስኳቸው ግሩፖች አስፈላጊውን መረጃዎች ፣ ማለስለሻዎች ፣ ኮንዶሞች እና ሌሎችም መሳሪያዎች አቅርቦት አላቸው ፣ ወይም አቅርቦቱን ያለማቋረጥ ለመስጠት እየጣሩ ይገኛሉ ፣ በተጨማሪም ባላቸው አቅም ዜጎች ተመርምረው ፣ ጤናቸውን አውቀው ፣ ከተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች እና ኤች አይቪ ተጠብቀው ፣ ተጠቂዎችንም በተገቢው የህክምና ሂደት ውስጥ በማስገባት ፣ ጤናማ ህይወትን እንዲመሩ የሚያስችል ፕሮግራም ቀርፀው እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ ስለዚህ እርስ በርስ እየተደጋገፍን ፣ እየተማማርን ጤንነታችንን ፣ ደህንነታችንን አብረን እንጠብቅ እላለሁ፡፡ ሰዎች ቫዝሊን ወይም ሎሽን እንደ ማለስለሻ መጠቀም ማቆም አለባቸው፡፡ እነዚህ ቅባቶች ኮንዶምን የመቅደድ እድላቸው በጣም ከፍተኛ ስለሆነ ለተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች የማጋለጥ አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡፡
ቤን፡ አንባቢዎቻችን 1ዜጋ በፌስቡክ ፣ እንዲሁም አዲስ አሊያንስን በፌስቡክ ፣ በቴሌግራም እና ዌብሳይታቸው ላይ በመግባት የምትፈልጉትን መረጃዎች ወይም ድጋፎች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ለማስታወስ እወዳለሁ፡፡
ዊሊ፡ በተጨማሪም ከአዕምሮአዊ ጤና ጋርም የሚያያዝ ይመስለኛል፡፡ ብዙ ሰው ማንነቱን ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎ ለመኖር ሲቸገር ታያለህ፡፡ ፆታዊ ተማርኮን እንደ አንድ የምታልፍበት የህይወት ደረጃ አድርጎ የሚያስብ ሰው ብዙ ነው፡፡ እናም… “ከዚህ ላይፍ” እወጣለሁ .. የሚሉ እሳቤዎች በጣም አሉ፡፡ በዛ ላይም… በሚደርስብን ጫና እና መገለል ወይም ጥላቻ … ብዙ ሰው ተስፋ ወደ መቁረጥ ይደርሳል፡፡ እናም ጥንቃቄ ብዙም ቦታ አያገኝም፡፡
ቤን፡ ደስ ይላል፡፡ እስቲ ዳኒ…. አንተ ምን አይነት ደህንነቱ የተጠበቀ ወሲብ ለመፈፀም የሚረዱ ማቴሪያሎችን ትጠቀማለህ? ከየትስ ነው የምታገኛቸው፡፡
ዳኒ፡ እ… (ብዙ አስቦበታል) ይሄንን ጥያቄ ከመጀመሪያው አንስቶ ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ሴክስ ምንድን ነው? እንዴትስ አወቅሁ የሚለውን ጉዞዬን ባወራው ደስ ይለኛል፡፡ ለስሜቴ ስም ሰጥቼው ፣ ራሴን ካወቅኩ በኋላ እና ቅድም ከነገርኳችሁ የመጀመሪያ የሴክስ አጋጣሚዬ በኋላ ፣ ብዙም ለሴክስ ክፍት አልነበርኩም፡፡ እውነቱን ለመናገር ሁልጊዜ ንፁህ አለመሆኑ ፣ ምቹ አለመሆኑ ፣ ጤናማ አለመሆኑ … ምናምን ነበር የሚታየኝ፡፡ ያኔ ብዙም አላውቅም ነበር፡፡ ሮልህ ምንድን ነው ሲሉኝ ግራ ይገባኝ ነበር፡፡ ቶፕ ልሁን ቦተም ወይም ቨርስ አላውቅም ነበር፡፡ የትኛውን እንደሆንኩ ፣ የትኛው እንደሚመቸኝ ለማወቅ ምንም ልምዱ አልነበረኝም፡፡ አንድ ጊዜ ለአንዱ “በቃ ይደብረኛል … ቆሻሻ ነገር ነው” ብዬው ነበር፡፡ ትክክል እንዳልነበርኩ አሁን አውቃለሁ ፤ ያኔ ግን በቃ እውነቴን ነበር፡፡ ከዛ እንዴት ከሴክስ በፊት ንፅህናን መጠበቅ እንደሚቻል ፣ ስለ ሉብሪካንት… አሁን ከማውቃቸው ነገሮች አብዛኞቹን ነገረኝ፡፡
የዛን ወቅት ከ House of La Fabuleux አባላት ጋር የተዋወቅሁበት ጊዜ ነበር፡፡ እና ከነሱ ነበር ልጁ የነገረኝን ነገሮች … ኮንዶም ፣ ሉብሪካንት ምናምን ማግኘት የጀመርኩት፡፡ ከራሴም ተርፌ ለሚጠይቁኝ ሰዎች ማካፈል ጀመርኩ ምናምን፡፡
ቤን፡ House of La Fabuleux አሁንም አለ እንዴ?
ዳኒ፡ ሃሃሃሃሃ….
ቤን፡ እ…ሺ! ሌላ ጥያ…
ዳኒ፡ ትንሽ ግን ስለ House of La Fabuleux ማውራት እፈልጋለሁ፡፡ በግሌ …ለእኔ ብዙ ዓይኔን የገለጡልኝን አጋጣሚዎች ያገኘሁት ያኔ ፣ እዛ ስለሆነ፡፡ ለኔ በወቅቱ ከእኔ እና ጥቂት ከማወራቸው ወንድ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን በቀር የተለያዩ ማንነቶችን ያየሁበት ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቅሁበት ጊዜ ነበር፡፡ እዛ ስብስብ ላይ ወንዶች ብቻ አልነበሩም ፣ ሌዝቢያን ሴቶች ፣ ባይሴክሹዋል ሰዎች … ይግረምህ ብሎ ቀጦች ሁሉ ነበሩ፡፡ ለኔ በጣም አስደናቂ ነበር ፤ የሆነ ቤተሰብህን ያገኘህ አይነት ስሜት ነበር የተሰማኝ፡፡ የመጀመሪያ ጊዜ ሳገኛቸው ፣ የመጀመሪያዬ መሆኑን አውቀው እንኳን በሌላ ነገር አይደለም የቀረቡኝ … አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮችን ይመክሩኝ ነበር … እንዴት ከራሴ ጋር ተስማምቼ መኖር እንደምችል የተማርኩት ያኔ – ከነሱ ነው፡፡ ነፃነታቸው እና አቀራረባቸው ነፃ ሆኜ ራሴን እንድሆን ረድቶኛል፡፡
አንድ ጊዜ እንዲያውም ትዝ ይለኛል … ምናልባት እሳቸው አሁን ላያስታውሱት ይችላሉ…ግን ፋሪስ (ኩቺ) …. እሳቸውን እዛ ቤት ውስጥ ማየቱ ብቻ በቂ ነበር ፤ ራሳቸውን የሚያቀርቡበት መንገድ ፣ በራስ መተማመናቸው ፣ የሚያነሷቸው ሃሳቦች በጣም አስደንቆኝ ነበር፡፡ ብዙ ሰው ሌሎች ሰዎች ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን ሆነው ሲያይ ትንሽ ይደነግጣል ፤ እኔ ግን ራሴን መሆን የምችልበት ቦታ እንዳገኘሁ ነበር የተሰማኝ፡፡ እና… የዛን ለት እንግዳም ስለነበርኩ ብዙ አላወራም ነበር ፣ ነገር ግን ፋሪስ አጠገቤ መጥተው … ጨዋታውን እንድቀላቀል ጋብዘውኝ… ብዙ ብዙ አወርተውኝ ነበር፡፡ እንዴት ራሴን መውደድ እንዳለብኝ ፣ ስህተት እንዳልሆንኩ ፣ ስለ ሴፍ ሴክስ … በቃ ብዙ ብዙ የማላውቃቸውን ነገሮች አሳውቀውኛል፡፡ ከዛ በኋላ ነገሮች ቀላል ሆነውልኝ ነበር፡፡
(በር ተንኳኳ …… ጋሽ ቦቼ ቢኖ … ናቸው …. እጃቸውን እስኪታጠቡ እኛ ወሬአችንን ቀጥለናል)
ዊሊ፡ ስለ House of La Fabuleux ካነሳህ ዘንዳ … በዛው በእንደዚህ አይነት የጓደኝነት ስብስቦች ላይ ሁልጊዜ የሚነሳ ጥያቄ አለ፡፡ እኔም ብዙ ጊዜ የምጠየቃቸው ጥያቄዎች…. ሰዎች በጓደኝነት ሲሰበሰቡ ፣ አብረው ሲውሉ ፣ በተለይም አብረው ሲያድሩ .. ሁልጊዜ ወሲብ የሚፈፀም ፣ ሰው ሳይባዳ የማያድር የማይመስላቸው ሰዎች አሉ፡፡ ያ ነገር ግን ትክክል አይደለም፡፡
ዳኒ፡ እንዴ… በህይወታችን እኮ ብዙ የሚያስፈልጉን ነገሮች አሉ፡፡ በህይወታችን የምናገኛቸው፣ የሚያጋጥሙን ሁሉም ሰዎች እኮ የሆነ የሚሞሉልን ቀዳዳ አለ ፤ ያ ቀዳዳ ደግሞ ሁልጊዜ ቂጥ ወይም እምስ አይደለም፡፡ ወይም መሆን የለበትም፡፡ እኔ ከጓደኞቼ ጋር አብሬ የማመሸው ፣ የምጠጣው ወይም ምሽቱን የማሳልፈው ፣ ጥሩ ጊዜን ለማሳለፍ ፣ እና ለመጫወት ነው እንጂ ….
ቤን፡ በነገራችን ላይ የ House of La Fabuleux አንዱ አባል ተቀላቅሎናል!!! እንኳን ደህና መጣህ ቦቼ!
ቦቼ፡ ስለ ምንድን ነው የምታወሩት?
ዊሊ፡ ሴክስ
ቦቼ፡ ማይ ፌቨራይት ሰብጀክት!!!
ቤን፡ የደረስክበትን ተቀላቀል እንግዲህ፡፡፡
ቤን፡ ሌላ ምን አስተውላለሁ መሰላችሁ… ይሔ የቀጦችን የሴክስ አጓጉል ባህሎች እኛም ተግባራዊ አድርገናቸው የምንኖር ብዙ ነን፡፡ ለምሳሌ ወንዱ ኮንዶም ይዞ መገኘት አለበት የሚሉ ቀጦች እንዳሉ ሁሉ … እና ቶፕ የሆነው…
ዳኒ፡ ሁለቱም ወንዶች አይደሉ እንዴ! ሃሃሃሃሃ
ቤን፡ እኮ! ሃሃሃሃ …. ለምን ሁሉም ሰው ዝግጁ አይሆንም? ሁሉም ተዘጋጅቶ ወደ ብዱ ለምን አይሄድም? የአንዱ ብቻ ኃላፊነት ለምን ይሆናል? ….
(ሻይ ለማፍላት ወደ 10 ደቂቃ ያህል ተጨቃጨቅን)
ዊሊ፡ እሺ….ቦቼ … ሴክስ ላንተ ምንድን ነው? በተለይም ከዜግነት ፣ ከጥንቃቄ ፣ ከነፃነት እንዲሁም ከፈቃድ ጋር በማያያዝ ነበር እያወራን የነበረው፡፡
ቤን፡ አዎ፣ በተለይም ብዙ ጊዜ የሚባል ነገር አለ በኛ በዜጎች መሐል … ዜጋ ከሴክስ ሌላ ለምንም አይጠቅምም… ወይም ደግሞ ዜግነት ለሴክስ ብቻ ነው የሚባል የተሳሳተ አመለካከት አለ፡፡ እስኪ ጠቅለል አድርገህ አውራን፡፡
ቦቼ፡ እ…. ሴክስ ማለት ለኔ … የሰው ልጅ ያለው መሠረታዊ ፍላጎት ነው፡፡ የሚፈልገው ነገር ሳይሆን… የሚያስፈልገው ፡፡ ብዙ ሰው አቀላቅሎታል ብዬ የምለው … የሚያስፈልገውን ነገር እና ስሜቱን ነው፡፡ ስሜትን በጊዜ ሂደት የምታገኘው እና የምታሳድገው ነገር ነው ፤ የሚያስፈልግህ ነገር ግን ውስጥህ ያለ … ልክ እንደ ምግብ አስፈላጊህ ነገር ነው፡፡ ሴክስም እንደዛ ነው … ማንኛውም ሰው ሊያደርገው የሚችል ተፈጥሮአዊ ፍላጎቱ ነው፡፡
ዜግነት እና ሴክስ እንደ አንድ የሚታዩበት ምክንያት … በእኔ እምነት … ሰዎች ስሜቶቻቸው ላይ ስለማይሰሩ ነው፡፡ የሚሰማቸውን ስሜት ተቀብለው በስሜትነቱ አስተናግደው ፤ ከስሜታቸው ጋር አብረው ለመኖር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ሲቀሩ ፣ ራሳቸውን መቀበል ሳይችሉ ሲቀሩ የሚያዳብሩት ነገር ይመስለኛል፡፡ ስሜትህን እንደ ስሜትነቱ አምነህ ስትቀበል ነው ክፍት ሆነህ ነገሮችን ለያይተህ ፣ የምትፈልገውን አውቀህ ቀጣዩን ርምጃህን የምትወስነው እና ዝግጁ የምትሆነው፡፡
ዕውነት ነው የኛ የዜጋው ማህበረሰብ በሴክስ ጉዳይ ላይ በጣም አክቲቭ ነን ፣ በተለይም ወንድ ዜጎች …. በተፈጥሮም ወንዶች ወሲባዊ ህይወታቸው ላይ በጣም አክቲቭ እንደሆኑ አምናለሁ፡፡ ሁለት ወንዶች አብረው ሲሆኑ ደግሞ….
ቤን፡ እንዴ…. እኛ የምናውቀው ያው የወንዱን ስለሆነ ነው እንጂ… ሴቶችም ሆኑ ማንኛውም ሰው እኩል ወሲባዊ ስሜት ያለው ይመስለኛል፡፡
ቦቼ፡ ልክ ነህ እኮ…. ግን አስተዳደጋችንም ፣ ባህላችንም ሌላም ሌላም ወንዶች የተሻለ ነፃ ወሲባዊ ህይወት እንዲኖረው ጫና አሳድሮብናል እላለሁ፡፡ ስለ ሴክስ ለማወቅም ሆነ ለመሞከር ብዙ ጊዜ የሚቀድመው ወንድ ነው፡፡
ስለ ፈቃድ ወይም ኮንሰንት ካወራን ደግሞ…. ሃሳቡ ራሱ.. ምን ማለት እንደሆነ ራሱ ብዙ ሰው የሚያውቀው አይመስለኝም፤ ምክንያቱም ከአንድ ሰው ጋር ተኛህ ማለት የግድ ወሲብ መፈፀም አለብህ ማለት አይደለም፡፡ ድንገት መሽቶብህ … ጓደኛህ ጋር ልታድር ትችላለህ ፤ አብረህ አምሽተህ ከጓደኛህ ጋር ለማንጋት ልትሄድ ትችላለህ ፤ ያ ማለት ግን ግዴታ ሴክስ ይኖራል ማለት አይደለም – ሰዎች ይሄን መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡ ለመሞከር ብሎ እንኳን ጥያቄ ሲያቀርብ ያለህን የጥያቄውን አቀባበል ፣ ስሜትህን ብቻ ተረድቶ ፣ አይቶ እንኳን የማይመለስ ሰው አለ፡፡ ያ ልክ አይደለም፡፡ እንዲያውም … እኔ በግሌ … እንደ አነስተኛ የመድፈር ሙከራ ወይም ደፈራ … እቆጥረዋለሁ .. መሰለኝ፡፡ … ግን ብዙ ነገሮችን ከግምት ውስጥ ለማስገባት ስትሞክር … ያለውን ነባራዊ ሁኔታ … የመረጃዎች እጥረት ምናምን ስታይ … የኮንሰንት .. ወይም ፈቃድ መስመር የቱ ጋር እንደሆነም … ትንሽ ያደናግረኛል፡፡
ቤን፡ ትክክል ነህ…. አብዛኛውን ጊዜ ምን የመከራከሪያ ነጥቦች ይነሳሉ መሰለህ … ትክክል ናቸው አይደሉም የሚለውን … አልገባበትም፤ ግን …አሁንም ከቀጦች ወሲባዊ ህይወት እና አይነቶች የወረስናቸው ናቸው የምለው አንድ ነገር አለ ፤ የወረስናቸው ለማለት እንኳን ትንሽ ይከብዳል … ያው በግልፅ የምናውቀው ፣ እየተማርን ያደግነው ፣ እንድንኖረውም የሚጠበቅብን የተቃራኒ ፆታ ግንኙነት እና ወሲባዊ ህይወትን ስለሆን ፣ ነባራዊ ሁኔታችንን በዛ ቅርፅ እየቀረፅን መምጣታችን ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ እና… ይኼ የመግደርደር … በተለይም በስፋት መሬት ላይ የምንሰማው … “ቶፑ” ሲጠይቅ “ቦተሟ” ሁለት ሶስቴ ተግደርድሮ ከዛ … አሁንም “ቶፑ” አሽኮርምሞ ፣ አማልሎ … መጨረሻ ላይ ጨክኖ እምቢ እንደማይለው የሚታመን ክፉ ልማድ አለ፡፡ እርግጥ ነው አልክድም… የሚወደው ሰው ይኖራል .. ያንን ጨዋታ የሚፈልግ ሊኖር ይችላል… ጨዋታውም በመሰረታዊ ሁኔታው ትክክል አይደለም እያልኩ አይደለም ፣ ግን እውነተኛ ፍላጎትን በግልፅ መነጋገር እና በሚያስማሟቸው ነገሮች ላይ ቢቀጥሉ የተሻለ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡
ቦቼ፡ እንደገና … አሁን ለምሳሌ … ፌስቡክ ወይም ግራይንደር ላይ አውርተህ … ተጀናጅነህ ለመገናኘት ተስማምተህ – ለሴክስም ሊሆን ይችላል – ከተገናኘህ በኋላ ፣ ላትመቻች ትችላለህ ፣ የሀሳብ ለውጥ ሊኖር ይችላል ፣ ወይም ደግሞ በተነጋገሩበት አይነት መንገድ ግንኙነታቸው ላይቀጥል ይችላል ፣ አንዱ ወገን እንደዛ አይነት ማንገራገር ካለው … ከዛ በኋላ የሚደረገው ወሲብ …ለእኔ በፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነው የሚል እምነት የለኝም፡፡ እና… ብዙ ስታስብበት … ትንሽ ያወዛግባል፡፡
ቤን፡ ዊሊ ብሮ!!! …. ሻይ ስታፈላ እኮ ዝም አልክ! ሃሃ …. እስቲ ያንተስ ሃሳብ
ዊሊ፡ ላስተናግዳችሁ እንጂ! ታናሻችን ነው ብላችሁ ታሰሩኛላችሁ …
ዳኒ፡ የኔ ግን ትንሽ አረቄ ያንሰዋል!!!
ዊሊ፡ ሰካራም! … እና ወደ ኮንሰንት ስንመለስ…. እኔ ትልቁ ችግራችን ኤክስፔክቴሽን ይመስለኛል፡፡ በሁለት ሰዎች ግንኙነት መሀል ሴክስ ይጠበቃል ፣ ግንኙነቱም ምንም አይነት ይሁን ምንም፡፡ ብዙ ጊዜ ሁለት የማይተዋወቁ ሰዎች ሲገናኙ ፣ ወሲባዊም ሆነ ስሜታዊ መሳሳቦች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ ለዛ ነገር ክፍት ሆኖ ከመቅረብ ይልቅ ሴክስ እንደሚኖር ጠብቆ ፣ እና አምኖ የመሄድ ነገር አለ፡፡ ከዛ የጠበቁት ሳይሆን ሲቀር…. ከዛ ሴክስ ትልቁ የመገናኛ ነገር ይሆንና ፣ ሰዋዊ የሆነውን ስሜት እያጣነው እንመጣለን፡፡ ነገሮች ወደሴክስ መርተው አይደለም ሴክስ ላይ የሚደረሰው ፣ መጀመሪያውኑ ሴክስ ታስቦበት ነው የሚመጣው፡፡ እርስ በርስ በመተዋወቅ ውስጥ ፣ ነገሮችን አብሮ በማድረግ ውስጥ ፣ ነገሮች ወደዛ ነገር እንዲመሩት እድል የመስጠት ነገር ብዙ አይታይም፡፡ ሁሉም እኔ እንዲህ ነኝ ፣ እኔ እንዲህ ነኝ ብሎ ቀድሞ ተገትሮ ስለሚመጣ ፣ ያንን ነገር አቀራርቦ ማጣጣም ትልቅ ስራ የሚፈልግ ነገር ነው፡፡ ያ ደግሞ ራስህን ማስደሰት ትተውና ለሰዎች ደስታን እና ፍላጎትን ለማሟላት የምታደርገው ስራ ነው የሚሆነው፡፡ እና እሱ ነገር ትልቅ ችግር ይመስለኛል፡፡
ዳኒ፡ … ህምምምም… ይመስለኛል … ቦቼ እንዳለው ትንሽ ግራ የሚያጋባ ሀሰብ አለው፡፡ ግን .. ሴክስ ወይም ወሲብ የሚባለው ሀሳብ በመሰረቱ .. ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ፈቃድን ያማከለ ነው፡፡ ሁለት ሰዎች ተስማምተው እና ፈቅደው የሚያደርጉት ነገር ነው ፡፡ መሆንም አለበት፡፡ የአንድ ወይም ከዛ በላይ ወገን መስማማት ከሌለበት ሴክስ መሆኑ ይቀርና ደፈራ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ… በቀላሉ ስታስበው … የሆነ ሬስቶራንት ሄደህ … ርቦህ ምግብ ታዛለህ … ይመጣልሃል መብላት ትጀምራለህ ፣ ከዛ አይጥምህም … ትተወዋለህ፡፡ ማንም መጥቶ አስገድዶ ብላ የሚልህ የለም፡፡ ሰው ሆነን ደግሞ ፍላጎቶቻችን በየጊዜው ይቀያየራሉ … ያንን ነገር ማክበር አለብን፡፡
ዊሊ፡ እኔ አንድ ገጠመኝ ነበረኝ፡፡ ከሆነ ሰው ጋር አወራን ፣ ለመገናኘት ተስማማን… እና ተገናኘን፡፡ ወሬአችን ፣ ጨዋታችን ጥሩ ሆኖ ሳለ ሴክስ ላይ ግን ባልጠበቅሁት መንገድ በጣም ኃይልን መጠቀም ጀመረ… ከዛ አልተመቸኝም ነበረና … ነገርኩት … ከዛ ወደ ማስገደድ ማዘንበል ጀመረ ፡፡ እኔ ደግሞ ጠብቄ ሄጄ የነበረው ያ ስላልነበረ … ተቃወምኩት፡፡ እና … ሴክስ ላይ እያለህ እንኳን የማይመችህ ከሆነ የማቆም መብት አለህ፡፡
ዳኒ፡ ደሞ ያለፈቃድ የሆነ ነገር ደግሞ … ሴክስን የመሰለ በጣም ኢንቲሜት የሆነ ነገር … ከዛ ሰው ፍላጎት ውጪ ስታደርግ እኮ… የዛንም ሰው ሙሉ ደስታ አታገኘውም እኮ…. አትደሰትበትም እኮ፡፡ ልስምህ እችላለሁ? ጡትሽን መንካት እችላለሁ? እያልክ ግዴታ መጠየቅ አለብህ ማለት አይደለም፡፡ አትኩሮትህን አጋርህ ላይ አድርግ ! በቃ! … የምታደርገው ነገር ያንን ሰው ምቾቱን እየነሳው ነወይ? የሰውነት ቋንቋው ምን ይለኛል? ይሄንን ለመረዳት ትኩረት መስጠት ነው፡፡ የሚያስደስተውን ነገር ለማወቅ መሞከር … ዘሎ ጉብ ከማለት፡፡ እኔ የማልወዳቸው ነገሮች ፣ ሰዎች እንዲያደርጉብኝ ፣ እንዲሉኝ የማፈልጋቸው ነገሮች እንዳሉ ሁሉ ፣ ያኛውም ሰው እነዛ ነገሮች ሊኖሩት ይችላሉና … ሁልጊዜ አጋራችን ላይ ትኩርት መስጠት አለብን፡፡
(ይቀጥላል … )
በዕውቀት የዜግነታችንን ክብር እንጎናፀፋለን!
#ዜጋ #ዕውቀት #መዝናኛ #የዜግነትክብር #ታሪክ #ማንነት #ጤና