ስለ እኛ

እኛ ማን ነን?

እንኳን በሰላም መጡ! ይህ በኢትዮጵያ የምንገኝ የኩዊር ማሕበረሰብ ለጋራ ዓላማችን በሕያውነት እና በሙሉ መሰጠት የምንቆምበት የበይነ-መረብ ቤታችን ነው። አሁን ሊጎበኙ የመጡት አንድ ድረ-ገጽ ብቻ ሳይሆን እርስ በርስ በመደጋገፍ ወደምናድግበት፣ ለመብቶቻችን ወደምንታገልበት እና ግንዛቤ ወደምንጨብጥበት ስፍራ ነው። በዚህ ድረ-ገፅ ላይ የሚያደርጉት እያንዳንዱ ቆይታ በሕብረት በመቆም አቅማችንን ለመገንባት በምናደርገው ጉዞ ውስጥ ውድ የሆነ ዋጋ አለው! በአንድነት የበይነ-መረብ አሻራችንን በማሳረፍ ጥንካሬን፣ መደጋገፍን እና በጋራ ጎልቶ መታየትን የሚያበለፅግ ከባቢን ለመፍጠር የምናደርገውን አስደሳች ጉዞ ይቀላቀሉ!

ከስያሜው በስተጀርባ ያለው ምንድን ነው?

directly translates to
“Dignity of
Citizenship”

first half of the very
first intro/ line of the
Ethiopian National
Anthem.

የዜግነት ክብር
Ye Zeginet
Kibir

To EMPHASIZE we,
the Ethiopian LGBTI+
community are still citizens
of the nation and claim our
rightful social conscience.

To DECONSTRUCT the
myth that the society
has for being a
member of LGBTI+
is a western influence.

As “Zega” is a code
name for the Ethiopian
LGBTI+ community, it is also
to EMPOWER the community
with dignity by portraying
its positive image.

የእኛ ተልዕኮ እና ራዕይ

ለኢትዮጵያ የኩዊር ማሕበረሰብ ዘላቂ ደኅንነት መረጋገጥ የሚጠቅሙ አገልግሎቶችን፣ መረጃዎችን እና ውሂቦችን ለማጠናቀር፣ ለማቀናበር እና ተደራሽ ለማድረግ ከሕብረተሰቡ ጋር በጋራ በመሥራት ኩዊር ግለሰቦች በቀስተ ደመና ባሸበረቀው ዓለም ውስጥ ቀና ብለው በኩራት ሲራመዱ ማየት!:

እኛ እምንሰራው

ሥነ-ጽሑፍ እና ሚድያ

ታሪክ ነጋሪ ጦማሮች
የምስል ቅንብር
የሩብ ዓመት የኩዊር ዲጂታል መጽሔት

ማሕበረሰባዊ ተደራሽነት

አውደ-ጥናቶች፣ ሥልጠናዎች፣ የሥራ ሥፍራዎች
ጥናት እና ምርምሮች
የአመራር እና የምክር አገልግሎት

ወሲባዊ እና የሥነ-ተዋልዶ ጤና እንዲሁም የአእምሮ ጤና ድጋፍ

የአባላዘር በሽታዎች ሕክምና እና ትስስር
የአእምሮ ጤና የምክር አገልግሎት
የድጋፍ ቡድኖች አገልግሎት